ተወልጄ ያደኩት በኢትዮጵያ ሜታ አቦ እየተባለች በምትጠራ ከአዲስ አበባ በአያ አምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኝ ትንሽ መደር ውስጥ ነው፤ ቤተሰቦቼ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ አላቸው ከሚባሉት ውስጥ ሲሆኑ ሁለቱም ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ ነበር፤ ስምንት ወንድሞችና ሁለት እህቶች ሲኖሩኝ እኔ ለቤተሰቦቼ ስድስተኛው ልጅ ነኝ፤ እድሜዬ ለትምህርት በደረሰ ግዜ የቄስ ትምህርት ቤት ገብቼ ፊደል ከመቁጠር አንስቶ እስከ ወንጌል ንባብ ድረስ ዘልቄ በዲማ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአንድ እስከ ስድስተኛ ክፍል በሙልጌታ ገድሌ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤት ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍሌን ካጠናቀኩ በኋላ በሰበታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ከዘጠኝ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ተከታትያለው ታድያ በዚህ ወቅት ነበር ለኪነ ጥበብ ያለኝን ዝንባሌ ማውጣትና መጠቀም የጀመርኩት በትምህርት ቤቱ የድራማና ሰዕነ ጽሑፍ ዘርፍ ውስጥ በመሳተፍ በግጥም በድምጻዊነት እና በድራማ በመሳተፍ ለሁለገብ ዝንባሌዬ ፈርመቅደድ የጀመርኩት ከዛም በኋላ በሰበታ የፀረ ኤድስ ክበብ ውስጥ አባል በመሆን በዝንባሌዬ እያዝናኑ በማስተማር ወጣቱ ትውልድ ስለአኤድ ያለውን ግንዛቤ እንዲጨምር በማድረግ ስራላይ የራሴን አስተዋጽሆ አበርክቻለው በመቀጠልም በሜጋ አንፊ ቲያትር ቤት የፒያኖ ሜጀር አጥንቼ የሁለገብ አርቲስት ካታጎሪ ተሸላሚ ሆኛለው በመቀጠልም የእውቀት አድማሴን ለማስፋት ኮሌጅ ገብቼ አኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጀመርያ አመት ተማሪ በነበርኩበት ወቅት ወደ አሜሪካ የመምጣት እድሉን አግኝቼ ጉዞዬን ወደ አገረ አሜሪካ አቀናው እዛም ትምህርቴን በመቀጠል በሲያትል ነርሲንግ አሲስታንት አኢንስቲትዉት የነርስ ረዳትነት ሰርተፊኬቴን በመቀጠልም ወደ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ በመአኤድ በነርሲንግ ዲፕሎማዬን ወደ ሲያትል በመመለስ በነርሲንግ ዲግሪዬን እየሰራው ጎን ለጎን በውስጤ ባለው የስነ ጽሑፍ ዝንባሌ በሲያትል በሚገኝው መክሊት የስህነ ጥበብ ማህበር ውስጥም አባል በመሆን በኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ በሲያትል በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያውጠነጥኑ ስራዎቼን እያቀረኩ ለኮሚኒቲዬ ያለኝን አስተዋጽሆ በማቅረብ ላይ እገኛለው ከዚህም በተጨማሪ በሲያትል ኪንግ ካውንቲ በፎር ካልቸር ፖትሪ ሆን በስ በሚባለው የሰዕነ ጽሑፍ ውድድር አሸናፊ ከነበሩት ጥቂት ኢትዮጵያውያን ውስጥ አንዱ በመሆን አገርን በማስተዋወቁ ረገድ የራሴን አስተዋጽሆ አበርክቻለው፤ አሁን ደግሞ ይህንን በቅርብ እርቀት ብቻ የተወሰነውን ስራዎቼን በሰፊው ለማዳረስ የመጀመርያ የግጥም መድብሌን በማሳታም ራሴን ህብረተሰቤን እና አገሬን ለዓለም የማሳውቅበትን መድረክ የመጀምርያውን እርምጃዬን ጀምሬያለው::
I born and raised in Ethiopia small town called Meta Abo, which found 25km away from the capital city Addis Ababa. My parent was a middle-class family they both worked in the beer factory near the village. I have six brothers and two sisters, and I am the sixth born child. When I get to a school-age, I went to the church priest who teaches the essential reading and writing, and then I went to an elementary school to continue from 1st to 8th grade. In my high school life, I got the opportunity to open my eyes to art. And I become a member of the art club and start to use my potential in music, acting and writing a poem. After high school, I become a member of an anti-aids club in the city of Sebeta and give awareness about aids for the youth. I took a piano class in Mega creative art center. When I graduate, I got the award of melty talented, and then I went to a different college to study information technology. When I was in my 1st year in college, I get an opportunity to come to the united states in 2008. I decided to study nursing, which differed from what I learn back home, and I went to a nursing assistant institute in shoreline, Washington. In 2011 I went to Angeles collage of nursing in Los Angeles California and earned my nursing diploma. In 2016 move back to Washington state while I am working as a practical licensing nurse to continue schooling for my nursing degree program. On the other hand, I keep my writing on spiritual and social issues. In 2018 I won poetry on buses in king county under the Amharic language category. Now is the right time for me to publish my first poetry book in Amharic language and I have a filing this is just the bagging, not the end.